ይህ ድረ-ገፅ የተማሪዎች መነሻ ገፅ ነው። በየዕለቱ የመምህራቸውን ፎቶ “ክሊክ” በማድረግ ከዚህ መነሳት አለባቸው። ከዚያም፣ ወደ መማሪያ ክፍላቸው ገፅ የሚወስዳቸው ሲሆን፣ ለዕለቱ ከሚያስፈልጓቸው መረጃዎች ጋር የሚያገናኙ ምስሎች ያገኛሉ።
የኢምፓክት አት ሆም ራዲዮ ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ከጠዋት ጀምሮ መልዕክት የሚያስተላልፍ ሲሆን፣ ተማሪዎች ከአንድ ተግባር ወደ ሌላ ተግባር እንዲሸጋገሩ የሚያሳስብ ነው። በመልዕክቶች መሀል ምንም አይነት ድምፅ ስለማያስተላልፍ፣ የ “ፖዝ በተን”ን መጫን አያስፈልግም። እኛም የምንመክራች ተማሪዎች ክፍት እንዲተውት እና በሬዲዮ የሚተላለፉ ጠቃሚ መልዕክቶችን እንዲከታተሉ እንጠይቃለን።
ተማሪዎች በተያዘላቸው መርሀ ግብር መሰረት “ዙም”ን ተጠቅመው ከመላው ክፍል፣ ከአነስተኛ ቡድን፣ እንዲሁም ከአጋዥ መምህራቸው ጋር 1-ለ-1 ውይይት ማድረግ ያስችላቸዋል። “ዙም”ን ለመጀመሪያ ጊዜ እንዴት መጠቀም እንዳለባችሁ እንዲሁም ድምፅ ማጥፋት እና ማብራት እንዴት እንደምትችሉ ለመማር ቪዲዮውን ይመልከቱ። ተማሪዎች የሚያስፈልጋቸውን የ “ዙም” ማስፈንጠሪያ “ሊንክ” ምንጊዜም በክፍላቸው ድረ-ገፅ ላይ ያገኛሉ።
ክሌቨር፣ ተማሪዎች ወደሚጠቀሟቸው አፕሊኬሽኖች በቀላሉ ለመግባት “ሳይን ኢን” ለማድረግ የሚያስችል ነው። ተማሪዎችም እያንዳንዱን ፖስዎርድ ማወቅ አይጠበቅባቸውም፤ አፕሊኬሽኖች “ክሌቨር”ን ሲጠቀሙ፣ አንድ ፖስዎርድ ብቻ ነው የሚያስፈልጋቸው።
ሌክሲያ መሰረታዊ የሆኑ የዕውቀት ክህሎቶችን ግልፅና ሲስተማቲክ በማድረግ እንዲሁም እያንዳንዱን ተጠቃሚ በአማከለ መልኩ የቀረበ ነው። ተማሪው የሌክሲያ የማስተማሪያ ተግባራት በሚጠቀምበት ጊዜ፣ ሶፍትዌሩ የተማሪውን ችሎታ ባገናዘበ መልኩ መምሪያ ይሰጠዋል። ተማሪ ልጅዎ በ ሌክሲያ ከተማረ በኋላ፣ የኢምፓክት መምህራን የልጅዎን የትምህርት አቀባበል መረጃ በመመልከት ለተማሪው ተስማሚ የሆኑ መምሪያዎችን ይሰጣሉ እንዲሁም በአነስተኛ ቡድኖች ውስጥ ለተማሪው እገዛ ያደርጋሉ።
አሚራ “ቨርችዋል” በሆነ መልኩ ምንባብ የሚያግዝ አስተማሪ ነው! ይህ በአይነቱ የመጀመሪያ ሲሆን፣ ተማሪ ልጅዎ ሲያነብ በማዳመጥ ድጋፍ የሚያስፈልገው ከሆነ ጣልቃ በመግባት ያስቆመዋል። አሚራ የልጅዎን አቅም ያገናዘቡ ታሪኮችን እንዲያነብ የሚጋብዝ ሲሆን ልጅዎ የሚወደውን ርዕስ መርጦ እንዲያነብ እድሉን ይሰጠዋል። አሚራ ልጅዎ ሲያነብ መንተባተቡን፣ የፊደል ግድፈቱን እንዲሁም አጠቃላይ የምንባብ ክህሎቱን በመገምገም ጥንካሬውን እና የሚሻሻሉ ነገሮችን ለመጠቆም ያስችላል። ልጅዎ ካነበበ በኋላ፣ የኢምፓክት መምህራን የልጅዎን አጠቃላይ የመማር ሂደት በመመልከት፣ ከልጅዎ ጋር በአነስተኛ ቡድኖች ውስጥ አብረው ሲሰሩ መረጃዎችን ተመርኩዘው ትክክለኛ መመሪያዎችን መስጠት ያስችላቸውል።
ድሪም-ቦክስ ፈታኝ የሆኑ፣ ደረጃቸውን የጠበቁና የትምህርት ስርዓቱን ተከትለው የተቀረፁ እና ለተማሪዎች የዕውቀት መዳበር የሚረዳ እንዲሁም ጥልቅ የሆነ የፅንሰ-ሀሳብ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያበረታታ ሲሆን ለአንድ ጥያቄ በተለያየ መንገድ መፍትሄ እንዲፈልጉ የሚያስችል ነው። ድሪም-ቦክስ በጨዋታ “ጌም” መልኩ የቀረበ እና ተማሪዎች የሚወዱት አቀራረብ ያለው ነው። ተማሪ ልጅዎ ድሪም-ቦክስ ላይ በተማረ ቁጥር፣ ፕሮግራሙ የተማሪውን ችሎታ በመለየት ለልጁ ተስማሚ የሆኑ እና ትክክለኛ ደረጃውን ያገናዘቡ መምሪያዎችን ያቀርባል።
ቼዝ አስደናቂ የ”ስትራቴጂ” ጨዋታ ሲሆን ሁሉም የኢምፓክት ተማሪዎች መማር የሚችሉበት ዕድል ያለው ነው። ቼዝ-ኪድ ተማሪዎችን እንዴት ቼዝ መጫወት እንደሚችሉ የሚያስተምር እና ችሎታቸውን እያሳደጉ ሲመጡ የእውነት መጫወት የሚያስችላቸው ነው።
ለ2ኛ ክፍል ብቻ
የኢምፓክት ተማሪዎች ጥሩ በሚባል ደረጃ የኮምፒውተር ክህሎት ያስፈልጋቸዋል ይሄውም መሰረታዊ ከሚባለው የፅሁፍ ክህሎት ይጀምራል! የፅሁፍ ክህሎት፤ ተማሪ ልጅዎ የ “ኦንላይን” ዓለምን በሚገባ ማሰስ እንዲችል ችሎታውን ከፍ የሚያደርግ ነው፣ ወደ 3ኛ ክፍል ሲዛወር መፃፍ፣ የሚያቀርባቸውን “ፕረዘንቴሽ”ን ማሟላት፣ ምርምር ማድረግ እንዲሁም በኮምፒውተር ኢሜይል እንዴት መላክ እንደሚችል ይማራል።
ለኪንደር-ጋርተን እና ለአንደኛ ክፍል ብቻ
የኢምፓክት ተማሪዎች ጠንካራ በሚባል ደረጃ የኮምፒውተር ክህሎት ያስፈልጋቸዋል ይሄውም መሰረታዊ ከሚባለው የፅሁፍ ክህሎት ይጀምራል! የፅሁፍ ክህሎት ተማሪ ልጅዎ የ “ኦንላይን” ዓለምን በሚገባ ማሰስ እንዲችል ችሎታውን ከፍ የሚያደርግ ነው፣ ወደ 3ኛ ክፍል ሲዛወር መፃፍ፣ ፕረዘንቴሽኖችን ማሟላት፣ ምርምር ማድረግ እንዲሁም በኮምፒውተር ኢሜይል ስለመላክ መማር ያስችላቸዋል።
ስለ ሳይንስ እና ማህበራዊ ጥናት ለማወቅ ይፈልጋሉ? ብሬንፖፕ ጄአር. ከኪንደር-ጋርተን እስከ 2ኛ ክፍል ድረስ ለሚሆኑ ተማሪዎች የመማሪያ ቪዲዮዎችን፣ ጌም፣ እንዲሁም ተግባራትን የያዘ ድረ-ገፅ ነው። ዋናው ገፅ በሚከተለው መልኩ ተከፋፍሏል፤ ሒሳብ፣ ማንበብ እና መፃፍ፣ ሳይንስ፣ ማህበራዊ ጥናት፣ ጤና፣ እንዲሁም ስነጥበብ እና ቴክኖሎጂ። በመጀመሪያ፣ ተማሪዎች ከስድስቱ ዋና የትምህርት አይነቶች ውስጥ አንዱን ይመርጣሉ። ያንን የትምህርት ዓይነት ሲመርጡ፣ ልዩ፣ ልዩ ወደሆኑ ምድቦች የሚከፋፈል ይሆናል። በእያንዳንዱ ምድብ ውስጥ፣ የተነጣጠሉ የቪዲዮ ርዕሶች እና ተግባራትን የያዘ ገፅ ይመጣል። ተማሪዎችም በዙሪያቸው ስላለው ዓለም ይበልጥ በተማሩ ቁጥር የተለያዩ ርዕሶችን መዳሰስ ይችላሉ።
ኮምፒውተር ሳይንስ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት እና ጥልቅ አሳቢነት በማበልፀግ ንቁ ተማሪዎች እንዲሆኑ የሚያስተምር ነው፣ ስለዚህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ፤ ልጆች የኮምፒውተር ሳይንስን የሚማሩበት ትክክለኛ ዕድሜ ነው። Code.org ለልጆች ተስማሚ የሆኑ ጨዋታዎችን በመጠቀም መሰረታዊ የ “ኮዲንግ” ክህሎት ያስተምራል።
ተማሪ ልጅዎ አዲስ ቋንቋ እንዲማር ወይም የእንግሊዝኛ ክህሎቱን እንዲያሻሽል ይፈልጋሉ? ዱዎሊንጎ 94 አይነት የተለያዩ ቋንቋዎችን መማር የሚያስችል ሲሆን ሁሉንም የክህሎት መጠን የሚመጥን ነው። በዓለም ላይ ከ300 ሚሊየን በላይ ሰዎች ቋንቋ ለመማር እንዲረዳቸው ዱዎሊንጎን ይጠቀማሉ። አዝናኝ እና ጌም-መሰል የትምህርት ይዘቶቹ ተማሪዎቹን ለማበረታታት እና ስለቋንቋው የበለጠ ጉጉ እንዲሆኑ የሚረዳ ነው። የዱዎሊንጎ ትምህርቶች እያንዳንዱን ተማሪ ያገናዘበ አስተያየት እና መልመጃ የሚሰጡ ሲሆን፣ የሚማሩትን ቋንቋ በደንብ እንዲያውቁ የሚያዘጋጃቸው ነው።